የህይዎት መርሆች

መርህዎች<<<<<<® ከመናገርህ በፊት→አስብ፣® ከመፈረምህ በፊት→አንብብ፣® ከማስተማርህ በፊት→ተማር፣® ከመምከርህ በፊት→ተግብር፣® ከመቁረጥህ በፊት→ለካ፣® ከማጉደልህ በፊት→ተካ፣® ከመዋጥህ በፊት→አላምጥ፣® ከመገንዘብህ በፊት→አድምጥ፣® ከማመንህ በፊት→አረጋግጥ፣® ከመረከብህ በፊት→ቁጠር፣® ከመወሰንህ በፊት→መርምር፣® ከመስራትህ በፊት→አቅድ፣® በትጋት ሳይሆን በብልሃት ስራ፣® ከመተኮስህ በፊት→አልም፣® ከመተቸትህ በፊት→አጣራ® ከመብላትህ በፊት→ስራ፣® ከመሞትህ በፊት→ነሰሃ ግባ፣® ከመሄድህ በፊት→ተስፋ ሰንቅ፣® ስትወያይ→ሁን አስተዋይ፣® ስትናደድ→ቶሎ ብረድ፣® ስትናገር→በቁምነገር፣® ስትቸገር→መላ ፍጠር፣® ስትቀመጥ→ቦታ ምረጥ፣® ስትወስን→ቆራጥ ሁን!!

ለተሻለ እኔ

ረሀብ ሆዱን ሲሞረሙረውና አላስተኛ ሲለው በብስጭት ብርድልብሱን ገፎ ተነሳ። ሰዓቱን ተመለከተ ‘ዘጠኝ ሰአት ተኩል’ ይላል. . . “ሆድን የፈጠረ አምላክ. . .” ብሎ ሊራገም ጀመረና ራሱን አቋረጠ። እንደነገሩ ለባብሶና ተጣጥቦ ከክፍሉ ወጣ። አጠገቡ ያለው ክፍል የምትኖረው እንስት በተለመደው የተኮሳተረ ፊቷ ተቀበለችው። እዚህ አገር ‘ጎረቤታምነት’ የሚባለው ነገር እሱ በሚያውቀው የጎረቤታምነት መንፈስ መልክ እንደሌለ የተገነዘበው ዘግየት ብሎ … Continue reading ለተሻለ እኔ

አረንጓዴ አሻራ……

.....እችን አይጥ እንትኗ ላይ ነበር ሀይላንድ ውሃ ማንጠልጠል( ጅራቷ ላይ)። ሌላው ይቅር በስንት መከራ የገዛሁትን ሶላር ትቁረጥብኝ!...ምነ ወገብሽ ቁርጥ ቢል እንደኔ ተስፋ። ይቺ ውሻ (ማለቴ አይጥ)! እሺ ማን ይሙት አሁን እዚህ ቢሮ ተገብቶ ገመድ ይበላል...ቲ! አርቴፊሻል አይጥ ነች...ወይ ደሞ ጠረ ልማት ናት። ተልዕኮ ያላት...(እህ የአይጥ አክቲቪስት ይኖረው ይሆንዴ?......)። ቢሮየን በትንሹ ልግለፅላችሁ....ከአንደኛ ክፍል እስከ አራተኛ ክፍል … Continue reading አረንጓዴ አሻራ……